Fana: At a Speed of Life!

አትሌት ትዕግስት በዓመቱ ምርጥ አትሌት ምርጫ የመጨረሻዎቹ ዕጩዎች ውስጥ ተካተተች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሴቶች ማራቶን የክብረ ወሰን ባለቤቷ አትሌት ትዕግስት አሰፋ በዓመቱ ምርጥ አትሌት ምርጫ የመጨረሻዎቹ አምስት ዕጩዎች ውስጥ ተካትታለች፡፡

በዓመቱ ምርጥ አትሌት ሽልማት ዘርፍ ቀደም ሲል 11 ዕጩዎች ለምርጫ የቀረቡ ሲሆን÷የዓለም አትሌቲክስ ዛሬ የመጨረሻዎቹን አምስት እጩዎች ይፋ አድርጓል፡፡

በዚህ ዝርዝር ውስጥም ኢትዮጵያዊቷ ትዕግስት አሰፋ፣ ኬንያዊቷ ፌ ኪፕዮገን፣ ኔዘርላንዳዊቷ ፌሚኬ ቦል፣ ጃማይካዊቷ ሸሪካ ጃክሰን እና ቬንዙዌላዊቷ ዩሊማር ሮጃስ በእጩነት ቀርበዋል፡፡

በዚሁ የሽልማት ዝርዝር ውስጥ ቀደም ሲል በ11ዱ እጩዎች ውስጥተካትታ የነበረችው አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ መቀነሷን የዓለም አትሌቲክስ መረጃ መላክታል፡፡

የዓመቱ ምርጥ አትሌት ሽልማት አሸናፊ በቀጣይ ሳምንት ይፋ እንደሚደረግ ተጠቁሟል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.