Fana: At a Speed of Life!

የፊፋ ዋና ፀሐፊ ለሥራ ጉብኝት ድሬዳዋ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም አቀፍ እግር ኳስ ማኅበር (ፊፋ) ዋና ፀሐፊ ፋጡማ ሳሞራይ ለሥራ ጉብኝት ማምሻውን ድሬዳዋ ገብተዋል፡፡

ዋና ፀሐፊዋ ማምሻውን ድሬዳዋ ዓለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር እና የአስተዳደሩ ካቢኔ አባላት አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ዋና ፀሐፊዋ በድሬዳዋ ቆይታቸው የሕፃናት የእግር ኳስ ፕሮጀክትና በስፖርት ዘርፍ የሚካሄዱ ተግባራትን እንደሚጎበኙ ይጠበቃል ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በተለይም በድሬዳዋ ስታዲየም በ50 ሚሊየን ብር ወጪ የመጫወቻ ሜዳውን ሰው ሠራሽ ሣር የማልበስና በስታዲየሙ የተሠሩ ሌሎች የልማት ሥራዎችን እንደሚመለከቱ ተገልጿል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.