Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ እና ሴራሊዮን በአቻ ውጤት ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ኢትዮጵያ እና ሴራሊዮን 0 ለ 0 በሆነ አቻ ውጤት ተለያዩ፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ የመጀመሪያ ጨዋታውን ዛሬ ከሴራሊዮን አቻው ጋር አከናውኗል፡፡

የሁለቱ ሀገራት ጨዋታ በሞሮኮ ኤል አብዲ ስታዲየም ምሽት 4 ሰዓት ላይ ተደርጓል፡፡

ጨዋታው በተከሰተ ጭጋጋማ አየር ምክንያት ለሶስት ጊዜ ተቋርጦ ነው የተጠናቀቀው።

በተካሄደው የማጣሪያ ጨዋታም ኢትዮጵያ እና ሴራሊዮን 0 ለ 0 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የምድብ ሁለተኛ ጨዋታውን በቀጣዩ ሳምንት ማክሰኞ ከቡርኪና ፋሶ አቻው ጋር የሚያከናውን ይሆናል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.