Fana: At a Speed of Life!

ሀድያ ሆሳዕና የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ አሸናፊ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀድያ ሆሳዕና ኢትዮጵያ ቡናን በመለያ ምት በማሸነፍ የ17ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ አሸናፊ ሆኗል፡፡

ሀድያ ሆሳዕናን እና ኢትዮጵያ ቡናን ያገናኘው የ17ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ጨዋታ መደበኛው ሰዓት 2 አቻ የተጠናቀቀ ሲሆን በተሰጠው መለያ ምት ነብሮቹ 5 ለ 4 አሸንፈዋል፡፡

በዚህም 17ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ተጋባዥ የነበረው ሀድያ ሆሳዕና በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫን ከፍ አድርጓል፡፡

አሸናፊው ሀድያ ሆሳዕና ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ጂራ ዋንጫውን ተረክቧል፡፡

ሁለተኛ ሆነው ላጠናቀቁት ቡናማዎቹ የብር ሜዳሊያ እንዲሁም ሶስተኛ ሆኖ ላጠናቀቀው ቅዱስ ጊዮርጊስ የነሀስ ሜዳሊያ መበርከቱን የአዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.