Fana: At a Speed of Life!

19ኛው የኢትዮጵያ ማራቶን ሪሌ ውድድር ነገ በመቐለ ይካሄዳል

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 14 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 19ኛው የኢትዮጵያ ማራቶን ሪሌ ውድድር በነገው እለት በትግራይ ክልል መቐለ ይካሄዳል።
 
በውድድሩ ከስምንት ክለቦች፣ አምስት ክልሎችና ከከተማ መስተዳደሮች የተውጣጡ 84 አትሌቶች ይካፈላሉ።
 
የማራቶን ሪሌ ውድድር ስድስት አትሌቶች ከአንድ ክለብ ወይም ክልል የሚሳተፉበት የውድድር ዓይነት ሲሆን ከ150 በላይ ልዑካን በውድድሩ ለመሳተፍ መቐለ ገብተዋል።
 
በሁለቱም ፆታዎች አንደኛ ለሚወጡ አትሌቶች ለእያንዳንዳቸው የ40 ሺህ ብር፣ ሁለተኛ 20 ሺህ ብር እንዲሁም 3ኛ ለሚወጡት ደግሞ የ15 ሺህ ብር ለሽልማት ተዘጋጅቷል።
 
ከማራቶን ሪሌይ ውድድሩ በተጨማሪ የፌዴሬሽኑ 27ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤም በዚያው ይካሄዳል ።
 
በ2015 ዓ.ም 18ኛው የኢትዮጵያ የማራቶን ሪሌይ ውድድርና የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ በሰመራ መካሄዱ ይታወሳል።
 
በወርቅነህ ጋሻሁን
 
 
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.