Fana: At a Speed of Life!

19ኛው የኢትዮጵያ ማራቶን ሪሌ ውድድር በመቀሌ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 19ኛው የኢትዮጵያ ማራቶን ሪሌ ውድድር በመቀሌ ከተማ መካሄድ ጀምሯል፡፡

በውድድሩ ከዘጠኝ ክለቦች፣ ሥድስት ክልሎችና ከተማ መሥተዳደሮች የተውጣጡ 84 አትሌቶች እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡

በሁለቱም ጾታዎች 1ኛ ለሚወጡ አትሌቶች ለእያንዳንዳቸው የ40 ሺህ ብር፣ 2ኛ ለሚወጡ 20 ሺህ ብር እንዲሁም 3ኛ ለሚወጡት የ15 ሺህ ብር ለሽልማት መዘጋጀቱን ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በውድድሩ ማስጀመሪያ ሥነ-ሥርዓት ላይ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አሥተዳደር ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሌተናንት ጄኔራል ፃድቃን ገ/ትንሳኤ፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስት ዴዔታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት፣ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ ተገኝተዋል፡፡

በወርቅነህ ጋሻሁን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.