Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በ27ኛው የዓለም የኢንቨስትመንት ጉባዔ ላይ እየተሳተፈች ነው

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን በሕንድ ኒው ደልሂ እየተካሄደ በሚገኘው 27ኛው የዓለም የኢንቨስትመንት ጉባዔ ላይ እየተሳተፈ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ተመስገን ጥላሁን ኢትዮጵያን በመወከል በበጉባዔው ላይ እየተሳተፉ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በጉባዔው ላይም የኢትዮጵያን የኢንቨስትመንት ዘርፍ፥ ዘርፈ-ብዙ ዕድሎች እና አማራጮችን ምክትል ኮሚሽነሩ ማስተዋወቃቸው ተመላክቷል፡፡

ከተለያዩ ዓለም አቀፍ የኢቨስትመንት ፕሮሞሽን ኤጀንሲዎች ጋርም ምክክር ማድረጋቸውን የኢንቨስትመንት ኮሚሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

በጉባዔው የመጀመሪያ ውሎም ከኢንቨስትመንት ዘርፍ ጋር የተገናኙ በተለይም የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ስትራቴጂ እና የድጋፍና ክትትል ሥራዎች ላይ ያተኮሩ የዐቅም ግንባታ ሥልጠናዎች ተሠጥተዋል ተብሏል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.