Fana: At a Speed of Life!

የሜሲ መለያዎች በ10 ሚሊየን ዶላር

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አርጀንቲናዊው የእግርኳስ ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ በ2022ቱ የኳታር ዓለም ዋንጫ የለበሳቸው መለያዎች ለጨረታ ቀርበዋል፡፡

ከትላንት ጀምሮ በተከፈተው እና ዛሬ ምሽት ይጠናቀቃል በተባለው ጨረታ አርጀንቲናዊው ኮከብ በዓለም ዋንጫው የለበሳቸው መለያዎች 10 ሚሊየን ዶላር ወይም 8 ሚሊየን ዩሮ እንደሚሸጡ ተጠብቋል፡፡

የሜሲ 6 መለያዎች ለጨረታ የቀረቡ ሲሆን÷ሁለቱ በምድብ ጨዋታ፣ሁለቱ በምርጥ 16 እንዲሁም ሁለቱ ደግሞ በፍጻሜ ጨዋታዎች ላይ የለበሳቸው መለያዎች መሆናቸው ተመላክቷል፡፡

ጨረታው በአንድ ቀን ብቻ 6 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር የደረሰ ሲሆን÷የሜሲ መለያዎች ዋጋ ቀደም ሲል በጨረታ የተሸጡ የታዋቂ ስፖርተኞችን የመለያ ዋጋ ክብረ ወሰን ሊሰብር እንደሚችል ነው የተገለፀው፡፡

የሜሲ መለያዎች በ10 ነጥብ 1 ሚሊየን ዶላር የሚሸጡ ከሆነ ቀደም ሲል በ10 ነጥብ 091 ሚሊየን ዶላር የተሸጠውን የታዋቂውን የቅርጫት ኳስ ተጫዋች ማይክል ጆርዳን መለያ ክብረ ወሰን ያሻሽላል ተብሏል፡፡

በተመሳሳይ የሜሲ መለያዎች ከ7 ነጥብ 142 ሚሊየን ዶላር በላይ ከተሸጡ ደግሞ የሀገሩን የቀድሞ ኮከብ ዲያጎ አርማንዶ ማራዶና መለያ ሽያጭ ክብረ ወሰንን እንደሚያሻሽል ይጠበቃል፡፡

ማራዶና በፈረንጆቹ 1986 የዓለም ዋንጫ አርጀንቲና ከእንግሊዝ ባደረጉትና በእጁ ጎል ባስቆጠረበት ጨዋታ የለበሰው መለያ ለጨረታ ቀርቦ 7 ነጥብ 141 ሚሊየን ዶላር መሸጡን ዘጋርዲያን ስፖርት አስነብቧል፡፡

የኳታሩ የዓለም ዋንጫ የመጨረሻው ሊሆን ይችላል የተባለው ሊዮኔል አንድሬስ ሜሲ በዓለም ዋንጫው ከአርጀንቲና ብሄራዊ ቡድን ጋር ሻምፒዮን መሆን የቻለ ሲሆን÷ የኮከብ ተጫዋች ሽልማትን ማሸነፉም አይዘነጋም፡፡

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አርጀንቲናዊው የእግርኳስ ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ በ2022ቱ የኳታር ዓለም ዋንጫ የለበሳቸው መለያዎች ለጨረታ ቀርበዋል፡፡
ከትላንት ጀምሮ በተከፈተው እና ዛሬ ምሽት ይጠናቀቃል በተባለው ጨረታ አርጀንቲናዊው ኮከብ በዓለም ዋንጫው የለበሳቸው መለያዎች 10 ሚሊየን ዶላር ወይም 8 ሚሊየን ዩሮ እንደሚሸጡ ተጠብቋል፡፡
የሜሲ 6 መለያዎች ለጨረታ የቀረቡ ሲሆን÷ሁለቱ በምድብ ጨዋታ፣ሁለቱ በምርጥ 16 እንዲሁም ሁለቱ ደግሞ በፍጻሜ ጨዋታዎች ላይ የለበሳቸው መለያዎች መሆናቸው ተመላክቷል፡፡
ጨረታው በአንድ ቀን ብቻ 6 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር የደረሰ ሲሆን÷የሜሲ መለያዎች ዋጋ ቀደም ሲል በጨረታ የተሸጡ የታዋቂ ስፖርተኞችን የመለያ ዋጋ ክብረ ወሰን ሊሰብር እንደሚችል ነው የተገለፀው፡፡
የሜሲ መለያዎች በ10 ነጥብ 1 ሚሊየን ዶላር የሚሸጡ ከሆነ ቀደም ሲል በ10 ነጥብ 91 ሚሊየን ዶላር የተሸጠውን የታዋቂውን የቅርጫት ኳስ ተጫዋች ማይክል ጆርዳን መለያ ክብረ ወሰን ያሻሽላል ተብሏል፡፡
በተመሳሳይ የሜሲ መለያዎች ከ7 ነጥብ 142 ሚሊየን ዶላር በላይ ከተሸጡ ደግሞ የሀገሩን የቀድሞ ኮከብ ዲያጎ አርማንዶ ማራዶና መለያ ሽያጭ ክብረ ወሰንን እንደሚያሻሽል ይጠበቃል፡፡
ማራዶና በፈረንጆቹ 1986 የዓለም ዋንጫ አርጀንቲና ከእንግሊዝ ባደረጉትና በእጁ ጎል ባስቆጠረበት ጨዋታ የለበሰው መለያ ለጨረታ ቀርቦ 7 ነጥብ 141 ሚሊየን ዶላር መሸጡን ዘጋርዲያን ስፖርት አስነብቧል፡፡
የኳታሩ የዓለም ዋንጫ የመጨረሻው ሊሆን ይችላል የተባለው ሊዮኔል አንድሬስ ሜሲ በዓለም ዋንጫው ከአርጀንቲና ብሄራዊ ቡድን ጋር ሻምፒዮን መሆን የቻለ ሲሆን÷ የኮከብ ተጫዋች ሽልማትን ማሸነፉም አይዘነጋም፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.