Fana: At a Speed of Life!

የጎንደር ከተማ ከ46 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ ሰጠ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት አምስት ወራት ከ46 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ 113 ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ መስጠቱን የጎንደር ከተማ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ አስታወቀ።

ፕሮጀክቶቹ በሙሉ ዐቅማቸው ወደ ሥራ ሲገቡም ለ32ሺህ 352 ዜጎች የሥራ ዕድል እንደሚፈጥሩ ነው የተገለጸው፡፡

ፈቃድ የተሰጠባቸው ዘርፎችም÷ ምግብና ምግብ ነክ፣ ኬሚካልና ኮንስትራክሽን፣ እንጨትና ብረታብረት፣ ጨርቃ ጨርቅና ቆዳ መሆናቸው ተብራርቷል፡፡

በአምስት ወራት ውስጥም 8 ሺህ 328 ቶን የቅባት እህልና ሌሎች ምርቶችን ወደ ውጪ ገበያ በመላክ ከ12 ሚሊየን ዶላር በላይ ተገኝቷል መባሉን የአሥተዳደሩ ኮሙኒኬሽን መምሪያ መረጃ አመላክቷል፡፡

እንዲሁም 31 ሺህ 557 ሊኒየር ሜትር ቆርቆሮ እና 100 ሺህ 170 ሊትር ዘይት በሀገር ውስጥ ምርት በመተካት ከግማሽ ሚሊየን ዶላር በላይ ማዳን መቻሉ ተጠቁሟል፡፡

ባለፉት አምስት ወራትም ለ667 ሰዎች የሥራ ዕድል መፍጠር መቻሉ ተጠቅሷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.