Fana: At a Speed of Life!

በፕሪሚየር ሊጉ ድሬደዋ ከተማ ድል ቀንቶታል

አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 10ኛ ሳምንት የውድድር መርሐ ግብር ዛሬ ሁለት ጨዋታዎች ተካሂደዋል፡፡

ቀን 9 ሰዓት ላይ ድሬደዋ ከተማ እና ኢትዮጵያ መድን ያካሄዱት ጨዋታ 2 ለ 1 በሆነ ውጤት ተጠናቅቋል፡፡

የድሬደዋ ከተማን የማሸነፊያ ግቦች ቻርለስ ሙሰጌና ካርሎስ ዳምጠው ሲያስቀጥሩ÷የኢትዮጵያ መድንን ብቸኛ ግብ ደግሞ ወገኔ ገዛኸኝ አስቆጥሯል፡፡

በተመሳሳይ ምሽቱ 12 ሰዓት ላይ ባህር ዳር ከተማ እና ሀምበሪቾ ዱራሜን ያገናኘው ጨዋታ 0 ለ 0 በሆነ ውጤት ተጠናቅቋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.