Fana: At a Speed of Life!

የሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን የካሜሩን አቻውን 3 ለ 1 አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር በምድብ ሦስት የሚገኙት ሴኔጋል እና ካሜሩን ጨዋታቸውን አድርገዋል፡፡

ብሔራዊ ቡድኖቹ ያደረጉትን የምድብ ሁለተኛ ዙር ጨዋታ÷ እስማኤል ሳር በ16ኛው፣ ሀቢብ ዲያሎ በ71ኛው እና ሳዲዮ ማኔ በ95ኛው ደቂቃ ከመረብ ባሳረፏቸው ጎሎች ሴኔጋል ድል አድርጋለች፡፡

የካሜሩንን የማስተዛዘኛ ጎል ደግሞ ቻርለስ ካስቴሌቶ በ83ኛ ደቂቃ አስቆጥሯል፡፡

በመጀመሪያው አጋማሽ የሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን በሁለተኛው አጋማሽ ደግሞ የካሜሩን ብሔራዊ ቡድን በኳስ ቁጥጥር ብልጫ ወስደዋል፡፡

በጨዋታው አንድ የሴኔጋል እና ሦስት የካሜሩን ተጫዋቾች የቢጫ ካርድ ተመልክተዋል፡፡

ሴኔጋል ጨዋታውን ማሸነፏን ተከትሎም ወደ ጥሎ ማለፉ የተቀላቀለች ሁለተኛዋ ሀገር ሆናለች፡፡

የአፍሪካ ዋንጫ የውድድር መርሐ-ግብር ምሽቱን ሲቀጥልም 5፡00 ላይ ጊኒ ከጋምቢያ ይገናኛሉ፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.