Fana: At a Speed of Life!

በታታ ሙምባይ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀናቸው

አዲስ አበባ፣ ጥር 12፣ 2016 ( ኤፍ ቢ ሲ) በህንድ በተካሄደ የታታ ሙምባይ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከአንድ እስከ ስምንተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀቁ፡፡

በሴቶች ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከአንድ እስከ ስምንተኛ ደረጃ በመያዝ ያጠናቀቁ ሲሆን ÷አበራሽ ምንሰዎ ፣ሙሉሃብት ፅጌ እና መድህን በጀኔ ከአንደኛ እና ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ አሸንፈዋል፡፡

አይን አዲስ ተሾመ፣አበራሽ ደምሴ፣አንቺ አለም ሃይማት፣አያንቱ ገመቹ እና ፋንቱ ገለሳ ደግሞ ከአራት እስከ ስምንተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቅቀዋል፡፡

በወንዶች ውድድርም ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከአንድ እስከ ሦስተኛ ደረጃ በመያዝ አሸንፈዋል፡፡

በዚህም ሀይሌ ለሚ ውድድሩን በአንደኝነት ሲያጠናቅቅ ሃይማኖት አለው እና ምትኩ ጣፋ ሁለተኛ እና ሦስተኛ በመሆን አጠናቅቀዋል፡፡

 
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.