Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ከኮሎምቢያ የዓለም ዋንጫ ውጭ ሆነች

አዲስ አበባ፣ ጥር 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የመጨረሻ ዙር ጨዋታውን ከሞሮኮ አቻው ጋር አድርጓል፡፡

ዛሬ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም የተደረገውን የመልስ ጨዋታ ኢትዮጵያ በፀሐይነሽ ጁላ ጎል ሞሮኮን 1 ለ 0 ብታሸንፍም÷ በድምር ውጤት 2 ለ 1 ተሸንፋ ከኮሎምቢያው የዓለም ዋንጫ ውጭ ሆናለች፡፡

ብሔራዊ ቡድኑ ከሣምንት በፊት ከሜዳው ውጪ ያደረገውን የማጣሪያ የመጀመሪያ ጨዋታ በሞሮኮ 2 ለ 0 መሸነፉ ይታወሳል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የዛሬውን ጨዋታ በድምር ውጤት ቢያሸንፍ በቀጥታ ኮሎምቢያ ለምታዘጋጀው የ2024 ዓለም ዋንጫ ውድድር ማለፍ ይችል ነበር፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.