Fana: At a Speed of Life!

ሞሮኮ እና ዲሞክራቲክ ኮንጎ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታ ሞሮኮ እና ዲሞክራቲክ ኮንጎ አንድ አቻ ተለያይተዋል፡፡

11 ሰዓት ላይ በተካሄደው የምድብ 6 ጨዋታ ለሞሮኮ አሽራፍ ሀኪሚ እንዲሁም ለዲሞክራቲክ ኮንጎ ካቶምፓ ሙቩምፓ ጎሎቹን አስቆጥረዋል፡፡

ዲሞክራቲክ ኮንጎ ያገኘቻትን የፍፁም ቅጣት ምት አጥቂው ሴድሪች ማካምቡ ሳይጠቀምበት ቀርቷል፡፡

የአፍሪካ ዋንጫ የቡድን ማጣሪያ መርሐ-ግብሮች ሲቀጥሉ÷ 2 ሰዓት ላይ ዛምቢያ ከታንዛኒያ እንዲሁም ደቡብ አፍሪካ ከናሚቢያ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.