Fana: At a Speed of Life!

በድሬዳዋ ከ38 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ አልሚዎች ፈቃድ ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፈው ግማሽ ዓመት ከ38 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ባላይ ካፒታል ላስመዘገቡ ባለሐብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ መስጠቱን የድሬዳዋ ከተማ አሥተዳደር ንግድ፣ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ አስታወቀ፡፡

ለ250 ባለሐብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ ለመስጠት ታቅዶ ለ244 መሰጠቱን የቢሮው የኢንቨስትመንት ጥናትና ፕሮሞሽን ቡድን መሪ አበራ መንግሥቱ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡

87 ባለሐብቶች በማምረቻ፣ 140 በአገልግሎት፣ 13 በግብርና እንዲሁም አራቱ በኮንስትራክሽን ዘርፎች ፈቃድ መውሰዳቸውንም አብራርተዋል፡፡

ፕሮጀክቶቹ ወደ ሥራ ሲገቡም ከ19 ሺህ ለሚልቁ ዜጎች ጊዜያዊና ቋሚ የሥራ ዕድል እንደሚፈጥሩ አመላክተዋል፡፡

ከዚህ በፊት የኢንቨስትመንት ፈቃድ ወስደው ወደ ሥራ ያልገቡ አልሚዎች ወደ ሥራ እንዲገቡ በተሰጠ አቅጣጫ መሰረት 88 ባለሐብቶች መለየታቸውን አስታውሰው÷ የክትትልና ቁጥጥር ሥራ እየተሠራ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

በተሾመ ኃይሉ

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.