Fana: At a Speed of Life!

በቆዳና ሌጦ ወጪ ንግድ የሚስተዋለውን ኮንትሮባንድ ለመከላከል ይሠራል – ሚኒስቴሩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በቆዳና ሌጦ ወጪ ንግድ ላይ የተያዘው ዕቅድ እንዳይሳካ ኮንትሮባንድ እንቅፋት ሆኖብኛል ሲል የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በተያዘው በጀት ዓመት የመጀመሪያ አጋማሽ 57 ሺህ 142 ቆዳ ለውጭ ገበያ በማቅረብ 400 ሺህ ዶላር ለማግኘት መታቀዱን በሚኒስቴሩ የእንስሣት እና እንስሣት ተዋጽኦ ወጪ ንግድ ግብይት ዴስክ ኃላፊ አበበ ታደሠ ገልጸዋል፡፡

38 ሺህ 122 የከብት ቆዳ ወደ ናይጄሪያ እና ቶጎ በመላክ 203 ሺህ ዶላር መገኘቱንም ተናግረዋል፡፡

መፈጸም የተቻለው የዕቅዱን 50 ነጥብ 7 በመቶ መሆኑንም ነው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የገለጹት፡፡

ዕቅዱ እንዳይሳካ ያደረጉት ምክንያቶችም የጥሬ ቆዳ ኮንትሮባንድ እና በጥሬ ቆዳ ወጪ ንግድ ላይ 150 በመቶ ቀረጥ መኖሩ እንደሆነም አመላክተዋል።

በመሆኑም ባለፈው ግማሽ ዓመት ያልተፈጸመውን በቀጣዩ ስድስት ወር ዕቅድ በማካተት ይሠራል ነው ያሉት፡፡

በሀገር ውስጥ የተጠናከረ የቆዳና ሌጦ ግብይት ስርዓት መዘርጋት እና ከጉምሩክ ኮሚሽን ጋር በመሆን በሞያሌ አካባቢ በሚስተዋለው የቆዳና ሌጦ ኮንትሮባንድ ላይ የቁጥጥር ሥራን ለማጠናከር እንሠራለን ነው ያሉት፡፡

በዮሐንስ ደርበው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.