Fana: At a Speed of Life!

ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሐመድ ከጅግጅጋ ከተማ ነጋዴዎችና ነዋሪዎች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሙስጠፌ መሐመድ ከጅግጅጋ ከተማ ነጋዴዎችና ነዋሪዎች ጋር በንግዱ ዘርፍ በሚታዩ ክፍተቶችና ሕገ ወጥ ንግድ ችግሮች ዙሪያ ተወያይተዋል።
በመድረኩ ላይ የተሳተፉ የጅግጅጋ ከተማ ነዋሪዎችና ነጋዴዎች ከንግድ በተያይዞ ላነሷቸው ቅሬታዎችና ጥያቄዎች ርዕሰ መስተዳደሩ ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በውይይቱ የኮትሮባንድ ንግድን ለመከላከል የጋራ መግባባት ላይ መደረሱን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
በውይይቱ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ሀላፊዎችን ጨምሮ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.