Fana: At a Speed of Life!

ከ21 ሚሊየን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅርንጫፍ አማካኝነት በተደረገ ክትትል 21 ሚሊየን 963 ሺህ 500 ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የገቢ እና ወጪ ኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ፡፡

የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ የተያዙት ከሶማሊያ ወደ ጅግጅጋ ከተማ ሊገቡ ሲሉ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ዕቃዎቹም የጉምሩክ ሥርዓት ያልተፈጸመባቸው መሆናቸውን የገቢዎች ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

የኮንትሮባንድ እና ሕገ-ወጥ ንግድን ለመከላከል እንዲቻል ባለድርሻ አካላትና ሕብረተሰቡ የበኩላቸውን ርብርብ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.