ጀርመን ለ8 ሆስፒታሎች 3 ነጥብ 6 ሚሊየን ዩሮ ዋጋ ያለው የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገች
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጀርመን መንግሥት በጀርመን ልማት ባንክ አማካይነት ለስምንት የማስተማሪያ ሆስፒታሎች 3 ነጥብ 6 ሚሊየን ዩሮ ዋጋ ያለው የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።
ድጋፍ የተደረገው ለጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝይድ ሆስፒታል፣ ድል ጮራ ሪፈራል ሆስፒታል፣ አዳማ ሪፈራል ሆስፒታል፣ ደሴ ሪፈራል ሆስፒታል፣ ፈለገ ሕይወት ሪፈራል ሆስፒታል፣ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ሜዲካል ማዕከል፣ አይደር ሪፈራል ሆስፒታልና ለአርባምንጭ ሪፈራል ሆስፒታሎች ነው፡፡
ከቁሳቁስ ድጋፉ በተጨማሪ ለሆስፒታሎቹ የአቅም ግንባታ ስልጠናና የቴክኒክ ድጋፍ እንደሚደረግም ተገልጿል።
ጀርመን በቀጣይም የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል መገለጹን ተቅሶ ኢዜአ ዘግቧል፡፡