Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል ከ500 ሺህ ኩንታል በላይ ምርጥ ዘር ለአርሶ አደሩ እየተሰራጨ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ከ500 ሺህ ኩንታል በላይ ምርጥ ዘር ተመርቶ ለአርሶ አደሩ እየተሰራጨ መሆኑን የክልሉ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ አስታወቀ።

ምርታማነታቸው ከፍተኛ የሆኑና በሽታን መቋቋም የሚችሉ ከ20 በላይ የሰብል ዓይነቶች ምርጥ ዘር እያመረተ መሆኑንም ኢንተርፕራይዙ ገልጿል።

የኢንተርፕራይዙ ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ ጫላ አበበ እንደገለጹት÷ ኢንተርፕራይዙ በክልሉ ከ80 በመቶ በላይ እንዲሁም በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ60 በመቶ በላይ ምርጥ ዘር ያቀርባል።

በኩታ ገጠም በተደራጁት አርሶ አደሮች፣ ባለሀብቶችና በራሱ የዘር ብዜት እርሻዎች በዚህ ዓመት ከ500 ሺህ በላይ ኩንታል እንደተመረተ የተገለጸ ሲሆን፥ ከዚህ ውስጥ 300 ሺህ ኩንታል ንጹህ ምርጥ ዘር ለስርጭት መዘጋጀቱ ተገልጿል፡፡

እስካሁን ከ60 ሺህ ኩንታል በላይ ምርጥ ዘር ለአርሶ አደሩ መሰራጨቱን አቶ ጫላ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ምርታማነትን ለማሳደግ ከሚያስችሉ ውስጥ አንዱ የሆነው ምርጥ ዘር በስፋት ለአርሶ አደሩ እንዲደርስ በትኩረት እየተራ መሆኑን ተናግረዋል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.