Fana: At a Speed of Life!

የ“ጽዱ ጎዳና – ኑሮ በጤና” ንቅናቄን በርካቶች እየተቀላቀሉ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕዝብ መፀዳጃ ቤቶችን በመገንባት ክብርን ጠብቆ የመፀዳዳት ባህልን ለማዳበር በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ይፋ የሆነውን የ“ጽዱ ጎዳና – ኑሮ በጤና” ንቅናቄን በርካቶች እየተቀላቀሉ ነው።

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር አቶ ተስፋዬ በልጂጌ፣ የስራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል፣ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) እና ሌሎች የመንግስት የስራ ሃላፊዎች በንቅናቄው የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ እየተሳተፉ ይገኛሉ።

ንቅናቄውን ተከትሎ ጽዱ ኢትዮጵያን ለመገንባት የሚውለውን በጀት ለማሰባሰብ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት በዛሬው ዕለት ዲጂታል ቴሌቶን አስጀምሯል።

በዚህም ብዙዎች በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተው ሂሳብ ቁጥር 1000623230248 የድርሻቸውን በማበርከት ላይ ይገኛሉ።

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.