Fana: At a Speed of Life!

የብልፅግና ፓርቲ የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ የስራ አፈፃፀም ግምገማ ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት ሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የብልፅግና ፓርቲ የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ የዘጠኝ ወራት የስራ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ ተጠናቋል።

በማጠቃለያ መርሐ ግብሩ የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ ሰማ ጥሩነህ (ዶ/ር)÷ ላለፉት ዓመታት ኢትዮጵያ የመጣችበት የፖለቲካ ስሪት የተወሳሰበ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡

የመጣውን ለውጥ የማይቀበሉትን በመታገል፣ ሕብረ–ብሔራዊ አንድነትን በማጠናከር መስራትና ህዝቡ በዕፎይታ ያለስጋት መደበኛ ስራውን እንዲያከናውን መስራት እንደሚገባም ገልፀዋል።

ስልጠናው በአመራሩና አባሉ የአመለካካት ልዩነት የነበረባቸው እንዲያርሙ ማስቻሉና አመራሩ እርስ በእርስ እንዲታዋወቅ ያደረገ እንዲሁም የፖለቲካ አቅም ቁመናውን በተግባር እንዲያሳይ ያገዘ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

በአንዳንድ ክልሎች የነበረውን የፀጥታ ችግር በዘላቂ ለመፍታት ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑን በመግለጽ፤ የህዝብ መድረኮችን በማዘጋጀት ጠቃሚ ግብዓቶችን መሰብሰብ መቻሉንም አንስተዋል፡፡

የዘጠኝ ወራቱ የክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የስራ አፈፃፀም እየተሻሻለ መሆኑን ጠቅሰው÷ በቀጣይ የዘርፉን ቀሪ ስራዎች ክልሎች በመተጋገዝ መስራት እንዳለባቸውም አሳስበዋል፡፡

ለቀጣይ ቀሪ ሁለት ወራት የትኩረት መስክ ስራ አቅጣጫዎች ስኬታማነት አቅም መፍጠር የሚችሉ የስራ መመሪያዎችንም ሰጥተዋል።

የአፈፃፀም ችግሮች እንዲታረሙ፣ በጥንካሬ የተነሱ ነጥቦች ይበልጥ ተጠናክረው እንዲቀጥሉ አመራሩ ህዝቡን በማሳተፍ መንቀሳቀስ እንደሚገባው መገለጹን የፓርቲው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.