Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል 6 ነጥብ 2 ሚሊየን ተማሪዎች የት/ቤት ምገባ ተጠቃሚ ሆነዋል – አቶ ሽመልስ አብዲሳ

 

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሁኑ ወቅት በኦሮሚያ ክልል 6 ነጥብ 2 ሚሊየን ተማሪዎች የትምህርት ቤት ምገባ መርሐ ግብር ተጠቃሚ መሆናቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ተናገሩ።

ርዕሰ መስተዳድሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ “የህዝባችን ህልም ልጆቹን በነባሩና በመጪው የዓለም ሥርዓት ውስጥ ተፎካካሪ ሆነው ማየት ነው” ብለዋል።

ለዚህም ልጆቹን ወደ ት/ቤት በመላክ ሳይወሰን ክፍተቶች ባሉባቸው ሁሉ ከመቀነቱ ፈትቶ ት/ቤቶችን በመገንባት እንዲሁም ከአውድማው እየዘገነ የተማሪ ምግብ ግብዓት በማቅረብ አላማውን በተግባር በመትለም ላይ ይገኛል ነው ያሉት።

የለውጡ መንግስትም ትውልድን ማስተማር ላይ ልዩ ትኩረት አድርጎ በስፋት በመንቀሳቀስ ላይ እንደሚገኝ አስገንዝበዋል፡፡

ህብረተሰቡ ባደረገው ተሳትፎ በአሁኑ ወቅት 6 ነጥብ 2 ሚሊየን ተማሪዎች የት/ቤት ምገባ መርሐ ግብር ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልፀው÷ ለተደረገው ትብብርም አመስግነዋል፡፡

የኦሮሞ ምሁራንም ሳይንስና ቴክኖሎጂ ታጥቆ ዓለም ላይ ተወዳዳሪ የሆነ ትውልድ በመገንባት ለህዝቡ አስተማማኝ ጋሻ ለመፍጠር በሚደረገውን እንቅስቃሴ “የድርጊት አርበኞች” እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.