Fana: At a Speed of Life!

አገልግሎቱ 715 ሺህ 324 ጉዳዮችን በማስተናገድ 1 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ አገኘ

 

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 715 ሺህ 324 ጉዳዮችን በማስተናገድ 1 ነጥብ 857 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት አስታውቋል፡፡

አገልግሎቱ ባለፉት 9 ወራት በተለያዩ ዘርፎች 715 ሺህ 324 ጉዳዮችን ያስተናገደ ሲሆን÷ለ1 ሚሊየን 237 ሺህ 329 ተገልጋዮች ደግሞ አገልግሎት መስጠት መቻሉ ተገልጿል፡፡

በሌላ በኩል 1 ሺህ 200 ሃሰተኛ ሰነዶች ጥቅም ላይ እንዳይውሉ መደረጉን የጠቆመው አገልግሎቱ÷ከእነዚህ ውስጥ 987 ሃሰተኛ የማንነት መታወቂያ ሲሆኑ 165ቱ ደግሞ ያላገባ ማስረጃዎች መሆናቸውን ጠቅሷል።

በተለያዩ አገልግሎት ዘርፎች 1 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ 1 ነጥብ 857 ቢሊየን ብር መገኘቱንም የአገልግሎቱ መረጃ ያመላክታል፡፡

ገቢው ከባለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ119 ሚሊየን ብር ብልጫ እንዳለው ነው የተገለጸው።

ወንጀልን በጋራ ለመከላከልም ከክልሎች፣ ከፌደራል ፖሊስ፣ ከአዲስ አበባ ፖሊስ እና ከተለያዩ የፍትሕ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.