በምንዛሬ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመተካት 3 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር ማዳን ተቻለ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ወደ ሀገር ውስጥ በውጪ ምንዛሬ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር በቀል ምርቶች በመተካት 3 ነጥብ 1 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ከብክነት ማዳን መቻሉን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ሚኒስቴሩ የ2016 በጀት ዓመት የ9 ወራት ዕቅድ አፈፃፀምን በተመለከተ ከሚኒስቴሩ ሥራ አስፈፃሚዎች እና ሠራተኞች ጋር እየተወያየ ነው፡፡
በዚህ ወቅትም የአምራች ኢንዱስትሪዎችን የማምረት አቅም ተግዳሮቶች ለመቅረፍ ከፍተኛ ጥረት በመደረጉ አበረታች ለውጥ መምጣቱ ተገልጿል ።
ገቢ ምርትን በመተካት ረገድም ከዚህ ፊት ወደ ሀገር ውስጥ በውጪ ምንዛሬ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር በቀል ምርቶች በመተካት 3 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር ከብክነት ማዳን መቻሉ ተጠቁሟል ።
ለዚህም መንግስት ለኢንዱስትሪ ዘርፍ ከፍተኛ ትኩረት መስጠቱ እና አዲስ የኢንዱስትሪ ፖሊሲ ተቀርጾ ወደ ትግበራ መግባቱ ከፍተኛ ሚና መጫዎቱን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡