ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) ወደ ኬንያ ያመሩበትን የአይ ዲ ኤ ጉባዔ አጠናቅቀው ወደ ኢትዮጵያ ተመለሱ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ወደ ኬንያ ያመሩበትን የአይ ዲ ኤ ጉባዔ አጠናቅቀው ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል።
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተመራ ልዑክ በኬንያ ናይሮቢ በተካሄደው ዓለም አቀፉ የልማት ማኅበር (አይ ዲ ኤ) 21ኛ የማሟያ ጉባዔ ላይ ተሳትፏል፡፡
በጉባዔውም ትምህርትን ተደራሽ በማድረግ ብሎም ወጣቶችን በማብቃት ኢትዮጵያ 2 ሚሊየን አዳዲስ ሥራዎችን ለመፍጠር ማለሟን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡
ጉባዔው የማኅበሩ ደጋፊዎችና ተባባሪ አካላት በአፍሪካ የልማት የገንዘብ ድጋፍ ቀዳሚ የትኩረት መስኮችን ለማመላከት እና አፅንዖት ለመስጠት ያለመ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡