Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል 812 ሚሊየን ብር የሚገመቱ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች በወጣቶች ተከናወኑ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል በዘንድሮ የበጋ ወቅት ከ812 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባራት በወጣቶች መከናወናቸውን የክልሉ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አስታወቀ።
 
የቢሮው ምከትል ሃላፊ አቶ ተሾመ ፈንታው እንደገለጹት÷በዘንድሮ የበጋ ወቅት ከ836 ሺህ በላይ ወጣቶችን በበጎ ፈቃድ አገልግሎት በማሳተፍ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ የልማት ሥራዎች ተከናውነዋል።
 
የበጎ ፈቃደኛ ወጣቱቹም 324 የአቅመ ደካማ ቤቶችን በአዲስ በመገንባትና በመጠገን፣ ደም በመለገስና 663 ደርዘን ደብተር ለችግረኛ ቤተሰብ ተማሪዎች ድጋፍ መደረጉን ተናግረዋል።
 
በተጨማሪም ከ104 ሄክታር በላይ የለማ የአቅመ ደካሞችን ሰብል በመሰብሰብና በበዓል ወቅት በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ለ27 ሺህ የህብረተሰብ ክፍሎች ማእድ ማጋራት መቻሉን አመልክተዋል።
 
በተፈጥሮ ሃብት ልማት ስራ በንቃት በመሳተፍ አበረታች ለውጥ ማስመዝባቸውን ጠቁመው÷ በሰላም ከማስከበር ባሻገር በጤና ላይ ያተኮረ ትምህርት ለህብረተሰቡ መስጠታቸውንም አስረድተዋል።
 
በተከናወነው የበጋ በጎ ፈቃድ አገልግሎት ከ812 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸው የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ የልማት ተግባራት በማከናወን ከ1 ነጥብ 3 ሚሊየን በላይ ህዝብ ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.