አቶ አደም ፋራህ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በ”ጽዱ ጎዳና-ኑሮ በጤና” ንቅናቄ እንዲሳተፍ ጥሪ አቀረቡ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ 20 ሺህ ብር በማበርከት “የጽዱ ጎዳና-ኑሮ በጤና” የዲጂታል ቴሌቶን ንቅናቄን ተቀላቅለዋል፡፡
በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረው “የጽዱ ጎዳና ኑሮ- በጤና” የዲጂታል ቴሌቶን ተሳትፎ የንቅናቄ መርሐ-ግብር ላይ በርካታ ኢትዮጵያውያን እየተሳተፉ እንደሚገኝ አቶ አደም ገልጸዋል።
በሁሉም ደረጃ የሚገኙ የብልጽግና ፓርቲ አመራር እና አባላት ተሳትፏቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ አበረታትዋል፡፡
አቶ አደም ሁሉም ኢትዮጵያዊ ያለ ምንም ልዩነት በዚህ የተቀደሰ ዓላማ ላይ እንዲሳተፍ ጥሪ ማቅረባቸውንም የፓርቲው መረጃ ያመላክታል፡፡