Fana: At a Speed of Life!

በሸገር ከተማ በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ የነበረ 510 ኩንታል ቡና ተያዘ

 

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሸገር ከተማ ፉሪ ክፍለ ከተማ በሁለት የጭነት ተሽከርካሪዎች በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ የነበረ 510 ኩንታል ቡና መያዙ ተገለፀ፡፡

የሸገር ከተማ የፉሪ ክ/ከ ፖሊስ መምሪያ አዘዥ ኮማንደር ፉፋ መገርሳ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳስታወቁት÷ በሀሰተኛ ሰነድ በሁለት የጭነት ተሽከርካሪዎች የተጫነ 510 ኩንታል ቡና ሲንቀሳቀስ ፉሪ አካባቢ ተይዟል፡፡

ቡናው መነሻው ቡኖ በደሌ ዞን ጨሮ ወረዳ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ከቡናው ጋር በቁጥጥር ስር የዋሉ አሽከርካሪዎች ላይ በጊዜ ቀጠሮ መዝገብ የምርመራ የማጣራት ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝም ጠቁመዋል።

በክፍለ ከተማው የወንጀል ተግባሮችን በመከታተል ረገድ የተጠናከረ ስራ እየተሰራ መሆኑን ኮማንደር ፉፋ አመላክተዋል፡፡

በታሪክ አዱኛ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.