Fana: At a Speed of Life!

ከ1 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር በሚልቅ ወጪ የተገነቡ ፋብሪካዎች ሥራ ጀመሩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በድሬዳዋ ከተማ አሥተዳደር ከ1 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር በሚልቅ ወጪ የተገነቡ ፋብሪካዎች ተመርቀው ወደ ምርት መግባታቸው ተገለጸ፡፡

“የኢትዮጵያ ታምርት፤ እኛም እንሸምት” 3ኛ ዙር ንቅናቄ በድሬዳዋ ከተማ ተጀምሯል፡፡

ንቅናቄውን ምክንያት በማድረግም የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል እና የድሬዳዋ አሥተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር ፋብሪካዎቹን መርቀው ሥራ አስጀምረዋል፡፡

ፋብሪካዎቹም የከባድ መኪና ተሳቢ ማምረቻ፣ የባለ ሦስትና አራት እግር የመኪና መገጣጠሚያ፣ የሕክምና ቁሶች ማምረቻ እና የታሸጉ ውኃ ፋብሪካዎች መሆናቸውን እና በዚህም ከ500 በላይ ለሚሆኑ ወገኖች ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ ዕድል መፈጠሩን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ድሬዳዋን የምሥራቅ የሀገሪቱ ክፍል የንግድና የኢንዱስትሪ ማዕከል የማድረግ ሂደት ጥሩ መንገድ ላይ እንደሚገኝም ከንቲባ ከድር ተናግረዋል፡፡

አሥተዳደሩ ለባለሀብቶች የሚያደርገውን ድጋፍና ማበረታቻ መቀጠሉንም አስረድተዋል፡፡

ባለፉት ሁለት ዓመታት በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ለባለሃብቶች የተደረገውን ድጋፍ ተከትሎም በኢንቨስትመንት ዘርፍ አመርቂ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.