Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለ1 ሺህ 455 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለ1 ሺህ 455 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ፡፡

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ÷ መጪውን የትንሳኤ በዓል ምክንያት በማድረግ የክልሉ መንግስት የይቅርታ አዋጁን መስፈርት ላሟሉ 1 ሺህ 455 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ ማድረጉን ተናግረዋል፡፡

ይቅርታ የተደረገላቸው የህግ ታራሚዎች በማረሚያ ቤት ቆይታቸው መልካም ሥነ-ምግባር ያሳዩ እና በሕግ በተደነገገው የይቅርታ መስፈርትን ማሟላታቸው በክልሉ የይቅርታ ቦርድ ተጣርቶ የቀረቡ ናቸው ብለዋል።

የይቅርታው ተጠቃሚዎች ይቅርታ በማያስከለክሉ ወንጀሎች ተሳትፈው በማረሚያ ቤት የቆዩ፣ በጤና ችግር፣ በዕድሜ መግፋትና ከሕጻናት ጋር አብረው የታሰሩ ፣ ከተፈረደባቸው አንድ ሶሥተኛና ከግማሽ በላይ የፍርድ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁ መሆናቸውን አስረድተዋል።

ይቅርታው ከተደረገላቸው ታራሚዎች መካከል 1 ሺህ 435 ቱ ከእስር የሚፈቱ ሲሆን÷ ቀሪ 20 ታራሚዎች የእስራት ጊዜያቸው የተቀነሰላቸው መሆኑን ገልጸዋል።

የይቅርታ ተጠቃሚ ከሆኑት የህግ ታራሚዎች መካከል 95ቱ ሴቶች እንዲሁም 1 ሺህ 360ዎቹ ደግሞ ወንዶች መሆናቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.