Fana: At a Speed of Life!

ምዕመኑ የትንሳኤ በዓልን ሲያከብር ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን በማገዝ እንዲሆን ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ምዕመኑ የትንሳኤ በዓልን ሲያከብር ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን በማገዝ ሊሆን እንደሚገባ የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስትያናት ካውንስል ዋና ጸሐፊ ቄስ ደረጄ ጀምበሩ አስገነዘቡ፡፡

ዋና ጸሐፊው ለትንሳኤ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመልዕክታቸውም÷ ምዕመኑ የትንሳኤ በዓልን ሲያከብር ዕርዳታና ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን ወገኖች በማገዝ ሊሆን ይገባል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በክርስቶስ ትንሳኤ ሁሉም በፍቅር ልብና በይቅርታ ለሰላምና አብሮነት በመጸለይ በዓሉን እንዲያከበርም ጠይቀዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.