Fana: At a Speed of Life!

በሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ የተከናወኑ ሥራዎችን ማጠናከር እንደሚገባ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐረሪ ክልል በሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ የተከናወኑ አበረታች ሥራዎች እንዲጠናከሩ የክልሉ ርዕሰ መሥተዳድር ኦርዲን በድሪ አሳሰቡ።

የክልሉ መሥተዳድር ምክር ቤት በክልሉ በሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ የተከናወኑ የ2016 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ዛሬ ገምግሟል።

በቀረበው ሪፖርትም በክልሉ÷ በልማት፣ በሰላምና በሌሎች መስኮች የተከናወኑ ሥራዎችን መረጃ ለማድረስ መሠራቱ ተገልጿል።

አቶ ኦርዲን በዚሁ ወቅት እንዳሉት÷ ባለፉት ዘጠኝ ወራት በሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ የተከናወኑ ሥራዎች አበረታች ናቸው።

በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ብሔራዊ መግባባት ከመፍጠርና ዴሞክራሲን በመገንባት ረገድ የተጀመሩ ሥራዎችን ማጠናከር እንደሚገባም ማሳሰባቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ዘርፉን በማጠናከርና በማዘመን በሕዝብና በመንግሥት መካከል ሁነኛ የመረጃ ድልድይ ሆኖ ተግባቦትን የማሳለጥ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውንም አስረድተዋል፡፡

ዘርፉን በስትራቴጂክ ዕቅድ የመምራት፣ መረጃን ለሕዝብ ተደራሽ የማድረግ እና በመረጃ የዳበረ ማኅበረሰብን የመፍጠር ሥራዎች እንዲጠናከሩም አሳስበዋል፡፡

በዘርፉ የሥራ ተነሳሽነትን በማሳደግና ተቋማዊ ግንኙነትን በማጠናከር ውጤታማ ለመሆን እንዲሠራም አስገንዝበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.