Fana: At a Speed of Life!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከእንግሊዝ አምባሳደር ጋር መከሩ

 

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በኢትዮጵያ ከእንግሊዝ አምባሳደር ዳረን ዊልች ጋር በሁለትዮሽ ግንኙነት ላይ ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም ÷በኢትዮጵያና እንግሊዝ ከተሞች መካከል የሁለትዮሽ ግንኙነትን በማጠናከር አብሮ ለመስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውን ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ አስፍረዋል፡፡

እንዲሁም ውይይቱ በአዲስ አበባ እየተከናወኑ በሚገኙ የልማት ስራዎች ላይ ትኩረት ያደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.