Fana: At a Speed of Life!

ኢጋድ በሶማሌ ክልል የአባል ሀገራቱን የከርሰ ምድር ውኃ ፕሮጀክት በይፋ አስጀመረ

 

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የምስራቅ አፍሪካ በይነ መንግሥታት ድርጅት (ኢጋድ) በሶማሌ ክልል የድርጅቱ አባል ሀገራት የከርሰ ምድር ውኃ ልማት ፕሮጀክትን በዛሬው ዕለት አስጀምሯል።

ፕሮጀክቱ በድርቅ፣ በማህበራዊ ልማት ውስንነቶችና በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ በቀጣናው ህብረተሰብ ላይ የሚፈጠረውን የውሃ እጥረት ችግር በዘላቂነት ለመፍታት ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

በማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ ÷ለበርካታ አመታት በዝቅተኛ ደረጃ ላይ የነበረውን የክልሉ ውሃ ሽፋን ከ47 በመቶ በላይ ማድረስ መቻሉን ተናግረዋል፡፡

የክልሉ መንግስት ከፌዴራል መንግሥትና ከሌሎች አጋር አካላት ጋር በመሆን የአርብቶ አደሩን ኑሮ ለማሻሻል ፣በተለይም የክልሉን ውሃ ሽፋን ለማሳደግ ተስፋ ሰጭ ሥራዎች እየሰራ መሆኑን መግለፃቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ሶማሌ ክልል በከርሰ ምድር ውኃ፤አመቱን ሙሉ በማይቋረጡ ወንዞች፤ ባልታረሰ ለም መሬትና በተፈጥሮ ጸጋዎች የታደለ ምድር መሆኑ ተመላክቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.