Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ 245 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ7 ሰው ህይወት አልፏል

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 5 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 24 ሰአታት ለ5 ሺህ 709 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 245 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።

ሚኒስትሯ በፌስ ቡክ ገጻቸው ቫይረሱ ከተገኘባቸው ውስጥ 241ዱ ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ፥ አራቱ የውጭ ሃገር ዜጎች መሆናቸውን አስታውቀዋል።

ቫይረሱ የተገኘባቸው ከ1 እስከ 85 አመት እድሜ የሚገኙ ሲሆን፥ 172 ወንድ እና 73 ሴቶች ናቸው ተብሏል።

ከዚህ ውስጥ 190 አዲስ አበባ፣ 17 ኦሮሚያ ክልል፣ 16 ሶማሌ ክልል፣ 15 ትግራይ ክልል፣ 4 ደቡብ እንዲሁም 3 ከአማራ ክልል ናቸው።

በተያያዘም በትናንትናው እለት 7 ሰዎች ከአዲስ አበባ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን፥ ይህም በአጠቃላይ በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎችን ቁጥር 47 አድርሶታል።

ህይወታቸው ካለፈው ውስጥ ስድስቱ በአስከሬን ምርመራ ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ሲረጋገጥ አንድ ግለሰብ በህክምና ማዕከል በህክምና ማዕከል የነበረ ነው ተብሏል።

በሌላ በኩል በትናንትናው እለት 17 ሰዎች ከቫይረሱ ያገገሙ ሲሆን፥ በሃገራችን ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 451 ሆኗል።

እስካሁን በኢትዮጵያ ለ170 ሺህ 860 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 2 ሺህ 915 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.