Fana: At a Speed of Life!

የተማሪዎች ነፃ ዝውውር ውሳኔ ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ቤት ለመመለስ ያለመ ነው – ትምህርት ሚኒስቴር

አዲስ አበባ ፣ ነሀሴ 7 ፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በትምህርት ሚኒስቴር የተላላፈው ከ 8ኛና 12ኛ ክፍል ውጪ ያሉ ተማሪዋች ነፃ ዝውውር ተማሪዋች ወደ ትምህርት ቤት እንዲመለሱ ለማበረታታት ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
 
የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ÷ ውሳኔው በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የትምህርት መርሃ ግብር ሲጀመር ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት እንዲመለሱ ለማበረታታት እና ወረርሽኙ የፈጠረውን ጫና ለመቀነስ የታሰበ ነው ብለዋል።
 
በአሁን ሰዓት ትኩረት ሰጥተን እየሰራን ያለነው ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ቤት መመለስ ላይ ነው ያሉት ሚኒስትሩ÷ በቀጣይም ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት ከተመለሱ በኋላ የትምህርት ጥራቱ ላይ በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል።
 
የትምህርት ጥራቱን በዘላቂነት ለመፍታትም በ 2014 ዓ.ም ወደ ተግባር የሚገባ አዲስ ስርዓተ ትምህርት እየተዘጋጀ መሆኑም ነው የገለጹት ።
 
በነፃ ዝውውር የተዘዋወሩ ተማሪዋች የትምህርት ምዕራፉ ሲጀመር በተዘዋወሩበት የትምህርት ክፍል ባለፈው የትምህርት ምዕራፍ ላይ ማካካሻ ወስደው ቀጣዪን የትምህርት መርሃ ግብር የሚቀጥሉ ይሆናል ማለታቸውን ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
 
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.