Fana: At a Speed of Life!

የዓለም ጤና ድርጅት እና ዩኒሴፍ በአፍሪካ ትምህርት ቤቶች ዳግም እንዲከፈቱ ጥሪ አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 15፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም ጤና ድርጅት እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የህጻናት አድን ድርጅት የአፍሪካ ሃገራት ትምህርት ቤቶችን ዳግም እንዲከፍቱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ድርጅቶቹ ረዘም ላለ ጊዜ ትምህርት ቤቶችን መዝጋት በተማሪዎች ላይ አሉታዊ ተፅእኖ እንደሚያስከትል ገልጸዋል፡፡

መንግስታት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እንዳይስፋፋ ንጽህና መጠበቅ የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታወችን መፍጠር ይገባልም ብለዋል፡፡

ተማሪዎቹ ረዘም ላለ ጊዜ ቤት ውስጥ ሲቆዩ ለምግብ እጥረት፣ ለቤት ውስጥ ጥቃት እና ያለ እድሜ ለሚከሰት እርግዝና እንደሚጋለጡም ገልጸዋል ፡፡

በአፍሪካ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ለህፃናት “ደህና ስፍራ” ናቸው ሲሉ የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ዳይሬክተር ማትሺዲሶ ተናግረዋል፡፡

እስካሁን ስድስት የአፍሪካ ሃገራት ብቻ ትምህርት ቤቶችን ሙሉ ለሙሉ ክፍት ሲያደርጉ አንዳንድ ሃገራት የተከፈቱ ትምህርት ቤቶችን በወረርሽኙ ዳግም መስፋፋት ምክንያት ዳግም ዘግተዋል፡፡

ሌሎችም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ፈተና ላይ እንዲቀመጡ ትምህርት ቤቶችን ክፍት ሲያደርጉ ኬኒያ በበኩሏ የትምህርት አመቱን ሙሉ በሙሉ ዝግ አድርጋለች፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.