Fana: At a Speed of Life!

የጃፓኑ ገዢ ፓርቲ የጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ ምትክ በመስከረም መጀመሪያ ሊመርጥ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 25፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የጃፓኑ ገዢ ፓርቲ ኤልዲፒ በመስከረም ወር መጀመሪያ የጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤን ምትክ ለመምረጥ ማቀዱን አስታወቀ።

የፓርቲውን የሊቀ መንበርነት ቦታ ለመያዝ አራት ተመራጮች መቀርባቸው ተነግሯል።

በዚህ መሰረትም ፓርቲው የመረጠው ሊቀመንበር በቀጥታ የጠቅላይ ሚኒስትርነቱን ቦታ ይይዛል ተብሏል።

እስከ አሁን በተሰበሰቡ የህዝብ አስተያየት መስጫዎች መሰረት የመከላከያ ሚኒስትሩ ሺጉሩ ኢሺባ የአቤን ቦታ ይተካሉ ተብሎ ይጠበቃል።

መከላከያ ሚኒስትሩ ተከታያቸውን በእጥፍ በመብለጥ በ34 በመቶ እየመሩ ሲሆን፦ ተከታያቸው ዮሺሂዳ ሱጋ በ14 በመቶ ይከተላሉ።

ሆኖም መከላከያ ሚኒስትሩ የህዝብ ድጋፍ ይኑራቸው እንጂ በገዢው ፓርቲ ያላቸው ድጋፍ አነስተኛ ነው ተብሏል።

የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ በህመም ምክንያት ሰሞኑን በገዛ ፍቃዳቸው ስልጣን መልቀቃቸው ይታወሳል።

ምንጭ፦ አልጀዚራ

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.