Fana: At a Speed of Life!

የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች የ2013 ዓ.ም በጀት ዓመት ዕቅድ ትውውቅ ማካሄድ ጀመሩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች የ2013 ዓ.ም በጀት ዓመት የፖለቲካ፣ የልማትና መልካም አስተዳደር ስራዎች ዕቅድ ትውውቅ በባህርዳር ከተማ መካሄድ ጀምሯል።
በዕቅድ ትውውቅ መድረክ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ፣የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ አገኘሁ ተሻገር እና ሌሎች አመራች ተገኝተዋል።
የክልል የዞንና የወረዳ ከፍተኛ አመራሮች በመሳተፍ ላይ የሚገኙ ሲሆን መድረኩ እስከ መጪው ሀሙስ እንደሚቀጥል ታውቋል።
የፖለቲካና ድርጅት ስራዎች መሪ ዕቅድ ውይይቱን ከመጀመሩ በፊትም በተለያዩ አካባቢዎች በግፍ ለተገደሉ የአማራ ብሄር ተወላጅ ወገኖቻችን የህሊና ፀሎት መደረጉን ከፓርቲው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.