የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ ከአዲሱ የአሜሪካ ተመራጭ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ጋር በስልክ ተወያዩ
አዲስ አበባ ፣ ህዳር 9 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የወቅቱ አፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር እና የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ ከአዲሱ የአሜሪካ ተመራጭ ፕሬዚዳንት ጆባይደን ጋር የአፍሪካ እና የአሜሪካን ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ተወያይተዋል ፡፡
ከዚህ ባለፈም የኮቪድ -19 ወረርሽኝን ለመቆጣጠር በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ መነጋገራቸውን ከፕሬዚዳንት ራማፎሳ ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ አመልክቷል።
ፕሬዚዳንት ራማፎሳ በውይይታቸው ወቅት በአፍሪካና በአሜሪካ መካከል ጠንካራ አጋርነት ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚሸጋገርም ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።
አዲሱ ተመራጭ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደንና ምክትላቸው ካማላ ሀሪስ አፍሪካ በዓለም አቀፍ ጉዳዮች የጎላ ሚና እንዳላት ተናግረዋል፡፡
ብዙ የአፍሪካ መሪዎች ጆ ባይደን በምርጫ በማሸነፋቸው የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ምንጭ፡-ቢቢሲ
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።