Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ታዬ ለተመድ ዋና ፀሃፊ የዘር ማጥፋት ወንጀል መከላከል አማካሪ በትግራይ ክልል እየተካሄደ ስላለው ህግን የማስከበር ዘመቻ ገለጻ አደረጉ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በተመድ የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ለመንግስታቱ ድርጅት ዋና ፀሃፊ የዘር ማጥፋት ወንጀል መከላከል አማካሪ ፕራሚላ ፓተን በትግራይ ክልል እየተካሄደ ስላለው ህግን የማስከበር ዘመቻ ገለጻ አደረጉ።

አምባሳደር ታዬ በዚህ ወቅት ጽንፈኛው የህወሓት ቡድን በመንግስት የቀረበውን የእንደራደርና የሽምግልና ጥያቄ ውድቅ አድርጎ የለውጥ ሂደቱን ለማደናቀፍ የሄደበትን መንገድ በተመለከተ ለአማካሪዋ ማብራሪያ አድርገውላቸዋል።

ከዚህ ባለፈም ቡድኑ በመላ ሃገሪቱ ብሄር ተኮር ግጭቶችን በማቀነባበር ያደረሳቸውን ጥፋቶች በተመለከተም አብራርተዋል።

አያይዘውም ቡድኑ በሰሜን እዝ የሃገር መከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት በመፈጸም ቀይ መስመር አልፏልም ነው ያሉት።

መንግስትም በትግራይ ክልል ህግና ስርአትን በማስከበር ወንጀለኞችን ለፍትህ ለማቅረብ ዘመቻ ጀምሯል ማለታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

የዋና ጸሃፊው የዘር ማጥፋት ወንጀል ዋና አማካሪ ፕራሚላ ፓተን በበኩላቸው፥ ለተደረገላቸው ገለጻ አመስግነው በንጹሃን ላይ የሚደርስ ጭፍጨፋን ማስቆም ይገባል ብለዋል።

አያይዘውም የህወሓት ጁንታ አሁን ላይ እየሄደበት ያለውን መንገድ አውግዘዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.