Fana: At a Speed of Life!

የሚዲያ ባለሙያዎች ትክክለኛ መረጃን ማቅረብ ለሰላም ግንባታ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው- ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል

አዲስ አበባ፣ ህዳር 24፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሚዲያ ባለሙያዎች በአስቸጋሪ ወቅቶች ኃላፊነት በተሞላበት መልኩ ትክክለኛ መረጃን ማቅረብ ለሰላም ግንባታ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል ገለፁ።

የአለም አቀፉ ማህበረሰብ እና የሚዲያ ሚና በቀውስ ጊዜ በሚል ርዕስ በሰላም ሚኒስቴር አመቻችነት የበይነ መረብ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል።

ውይይቱን የከፈቱት የሰላም ሚኒሰትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል፥ በወቅታዊው የሀገራችን ሰሜናዊ ክፍል ህግ የማስከበር ሂደትና ተዛማጅ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ከአለም ዓቀፍ እና የሀገር ውስጥ የሚዲያ ባለሙያዎች ጋር በዚህ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ውይይት መካሄዱ እጅግ ጠቃሚ ነው መሆኑንም አንስተዋል።

የሚዲያ ባለሙያዎች የሚዲያን ሰላም የማስፈንም ሆነ ጥፋት የማስከተል አቅም በሚገባ ተገንዝበው በተለይም በአስቸጋሪ ወቅቶች ጊዜ ኃላፊነት በተሞላበት መልኩ ትክክለኛ መረጃን የማቀበል ስራቸውን በአግባቡ መወጣታቸው ለሰላም ግንባታ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው አመልክተዋል።

በውይይቱ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ጌታቸው ድንቁ፣ ፕሮፌሰር አን ፊትስ ጄራለድ ከካናዳ፣ አቶ ድጋፌ ደባልቄ ከካናዳ እንዲሁም ቬነስ ናራያን ከለንደን በርዕሱ ዙሪያ ሀሳባቸውንና ልምዳቸውን ለተሳታፊዎች አካፍለዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.