Fana: At a Speed of Life!

በህግ ማስከበር ሂደቱ ጉዳት ያጋጠማቸው ወገኖች ያሉባቸው አካባቢዎች የሰብዓዊ ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገለጸ

አዲስ አበባ ፣ህዳር 29 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአላማጣ፣ መኾኒ፣ ጨረጨር፣ ዳንሻ፣ ማይካድራ እና ሌሎች በህግ ማስከበር ሂደቱ ጉዳት ያጋጠማቸው ወገኖች ያሉባቸው አካባቢዎች የሰብዓዊ ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠሉን የሰላም ሚኒስቴር አስታወቀ።
ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ድጋፍ ተቋማት ከሰላም ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋሙ ብሔራዊ አደጋ ስጋት ኮሚሽን ጋር በትብብር በርካታ የምግብና ቁሳቁስ ጭነት በዛሬው ዕለት ሽሬ ከተማ ማድረሳቸው ተገልጿል።
ስርጭቱ እንደየ ጉዳት መጠን ቅድሚያ እየተሰጠ በተደራጀ ሁኔታ እየተከናወነ እንደሚገኝም ተገልጿል።
ድጋፉ ማህበረሰቡን መልሶ እስከማቋቋም የሚዘልቅ ሲሆን የተደራሽነት ክትትል በሚመለከታቸው አካላት በአትኩሮት እየተካሄደ እንደሚገኝ ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.