Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት 24 ሰዓታት 526 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው 1 ሺህ 731 ሰዎች አገግመዋል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 5 ሺህ 741 የላቦራቶሪ ናሙና ምርመራ 526 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።
በአጠቃላይ እስካሁን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 115 ሺህ 360 መድረሱ ነው የተገለፀው።
በሌላ በኩል ባለፉት 24 ሰዓታት 1 ሺህ 731 ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ እስካሁን ድረስ 88ሺህ 975 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።
እንዲሁም በ24 ሰዓታት ውስጥ የ 10 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 779 ደርሷል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል
https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.