ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ከፈረንሳዩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 5 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ከፈረንሳይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዦ ኢቭ ለድሮዮ ጋር ተወያይተዋል፡፡
ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዛሬ ማለዳ ላይ በኮትዲቯሩ ፕሬዚዳንት አላሳኔ ኦታራ በአለ ሲመት ላይ ለመገኘት ወደ ስፍራው ማቅናታቸው ይታወሳል፡፡
የፈረንሳይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መንግስት በትግራይ ክልል ያካሄደውን የህግ ማስከበር ዘመቻ በተመለከተ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር መወያየታቸው የሚታወስ ነው።
በኮትዲቯር ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ከፈረንሳይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዦ ኢቭ ለድሮዮ ጋር ያደረጉት ውይይትም በዚሁ ጉዳይ ላይ ያተኮረ እንደነበር ኢቢሲ ዘግቧል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!