ጤና ሚኒስቴር በሲዳማ ክልል የጤና ልማት ግቦች እንዲሳኩ ድጋፍ እንደሚያደርግ ገለጸ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 24፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በሲዳማ ክልል የሚገኙ የጤና ተቋማትን ጎበኙ።
የጤና ሚኒስትሯ በክልሉ ሀዋሳ ከተማ የሚገኙ የአዳሬ ጠቅላላ ሆስፒታል እና በመሃል ክፍለ ከተማ የሚገኘውን የእናቶችና ሕፃናት ስፔሻሊቲ ሕክምና ማዕከልን ጎብኝተዋል።
በጉብኝታቸውም የጤና ተቋማትን ለህብረተሰቡ ተደራሽ በማድረግና የሚሰጠውን የጤና አገልግሎት ጥራቱን ከማሻሻል አኳያ እንደ ሀገር በርካታ ጥረቶች እየተደረጉ እንደሚገኙ መግለጻቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
በዚህ ወቅትም በጤና ተቋማቶቹ የአገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል እየተደረገ ያለው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም አሳስበዋል።
ጤና ሚኒስቴር ከክልሉ ጤና ቢሮ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን በክልሉ የተያዙ የጤና ልማት ግቦች እንዲሳኩ አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋልም ብለዋል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!