Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይን ጨምሮ አራት ኢትዮጵያውያን ከ100 የአፍሪካ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ውስጥ ተካተቱ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 27 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኒው አፍሪካ መፅሄት በፈረንጆቹ 2020 በአፍሪካ 100 ተፅዕኖ ፈጣሪዎችን ይፋ አድርጓል።

መፅህሄቱ ይፋ ባደረገው የ2020 የአፍሪካ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ውስጥ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረማሪያም ፣ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም እና በምስራቅና ደቡብ አፍሪካ የሚንቀሳቀሰው የንግድና የልማት ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አድማሱ ታደሰ ተካተዋል።

በመሪዎች ዘርፍ በቀዳሚነት የተቀመጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተጠናቀቀው የፈረንጆቹ ዓመት ተወዳጅ ከነበሩ ስሞች መከካል አንዱ ነበሩ ብሏል መፅሄቱ።

የኖቤል የሰላም ሽልማት ያሸነፉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ኢትዮጵያን ኢትዮጵያ ያደረጓትን የተለያዩ ብሄሮች እና ሀይማኖቶች አንድ ለማድረግ የሚያስችሉ የተለያዩ ተግባራትን አከናውነዋል ብለዋል።

በምስራቅ አፍሪካም ሆነ በአፍሪካ በኢኮኖሚው እና በፀጥታው ዘርፍ የወሳኝነት ሚና ያላት ኢትዮጵያ መሪ መሆናቸውን አንስቷል።

ሌላኛው ከ100 ተፅዕኖ ፈጣሪዎች መካከል በመሪዎች ዘርፍ የተካተቱት ኢትዮጵያዊ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ናቸው።

ዶክተር ቴድሮስ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ወቅት የዓለም ጤና ድርጅትን በመምራት በዓለም አቀፍ ደረጃ አፍሪካዊ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሆነዋል ብሏል መፅሄቱ።

በተለይ ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ በአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና በሌሎች አካላት ትችት ቢቀርብባቸውም ለምክንያታዊነት ታማኝ ድፅም ሆነዋል ሲል ገልጿቸዋል።

በዶናልድ ትራምፕ በተለያዩ መንገድ ወቀሳ ቢቀርብባቸውም ትኩረታቸውን ሳያጡ ስራቸውን ማከናወናቸውን እና ለቀረበባቸው ትችት በጨዋ ቃላት ምላሽ ሰጥተዋል ነው ያለው መፅሄቱ።

በተመሳሳይ በመሪዎች ዘርፍ ተፅዕኖ ፈጣሪ የሆኑት ኢትዮጵያዊ በምስራቅና ደቡብ አፍሪካ የሚንቀሳቀሰው የንግድና የልማት ባንክ ፕሬዚዳንትና ስራ አስፈፃሚ አቶ አድማሱ ታደሰ ናቸው።

አቶ አድማሱ ታደሰ የሚሙት የንግድና የልማት ባንክ የምስራቅና ደቡብ አፍሪካ ሀገራት የጋራ ገበያ አባል ሀገራትን የመደገፍ ግዴታን ይዞ የተቋቋመና አዲስ ምዕራፍ የከፈተ ነው ተብሏል።

በእርሳቸው ዘመን አስተዳደር የባንኩ ሀብት በ7 አጥፍ በማደግ 7 ቢሊየን ዶላር እንደደረሰ ተነግሯል።

ባንኩ ከበድ ያሉ አደጋዎችን ተጋፍጦ ስኬታማ መሆን እንደቻለም መፅሄቱ በዘገባው ላይ አስፍሯል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረማሪያም ሌሎች አየር መንገዶች በኮሮና ወረርሽኝ ወቅት ቀውስ ውሰጥ ሲገቡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተመሳሳይ ቀውስ ውስጥ እንዳይገባ አስችለዋል ሲል መፅሄቱ አስታውቋል።

በተለይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኮሮና ወረርሽኝ በተከሰተበት ቅፅበት አገልግሎቱን ወደ ካርጎ በመቀየር ሊከሰት የሚችለውን ቀውስ እንዲሻገር አስቸለዋል ነው ያለው።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳ
የፋና ድረ ቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.