Fana: At a Speed of Life!

ኮቪድ-19ን በመከላከል ላይ ያተኮረ ንቅናቄ ከጥር 3 ቀን ጀምሮ ለስድስት ወራት ይካሄዳል

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 30 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኮቪድ-19 ወረርሽኝን መከላከል ላይ ያተኮረ ንቅናቄ ከጥር 3 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚካሄድ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በዚሁ ጉዳይ ላይ የጤና ሚኒስቴር ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ጋር ተወያይቷል።

ለስድስት ወራት የሚቆየው ንቅናቄ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማስክ ማድረግን ጨምሮ የኮቪድ-19 መከላከያ ዘዴዎችን በአግባቡ በመተግበር ላይ ትኩረቱን ያደርጋል ተብሏል።

በእነዚህ ወራት “እንድናገለግልዎ ማስክዎን ያድርጉ” የሚል ንቅናቄ እንደሚካሄድ እና በንቅናቄው ወቅትና ከዚያም በኋላ የሚያገለግሉ ማስኮችን የማሰባሰብ ስራ እንደሚከናወን ተገልጿል።

ንቅናቄው በከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና ትምህርት ቤቶች፣ በአገልግሎት ሰጪ ተቋማት፣ በትራንስፖርት መናኸሪያ ስፍራዎች፣ በገበያ ቦታዎች፣ በሀይማኖት ተቋማትና ህዝብ በብዛት በሚሰበሰብባቸው መሰል ስፍራዎች ላይ ትኩረት እንደሚያደርግ ተጠቁሟል።

በንቅናቄው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትም በቁጥጥርና ክትትል ስራ እንዲሁም በግንዛቤ ማስጨበጥ ተግባር ላይ በኃላፊነት እንደሚንቀሳቀስ ኢብኮ ዘግቧል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.