Fana: At a Speed of Life!

የምክንያታዊ ወጣት መድረክ በለገጣፎ ከተማ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ጥር 4 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኦሮሚያ ክልል በለገጣፎ ለዳዲ ከተማ አስተዳደር የምክንያታዊ ወጣት መድረክ እየተካሄደ ነው።
የውይይት መድረኩ ”የሀገረ መንግስት ግንባታና የወጣቱ ሚና” በሚል ርዕስ የተዘጋጀ መሆኑ ተመላክቷል።
በመድረኩ ከከተማው የተውጣጡ ምሁራን ወጣቶች ተሳትፈውበታል።
በኢትዮጵያ ሰላምና ብልጽግና የተረጋገጠባት፣ ዜጎች በእኩልነት ተንቀሳቅሰውና ሰርተው ህይወታቸውን የሚመሩባት እንድትሆን ለማድረግና ሀገረ መንግስቱ ሊቆምባቸው የሚገቡ ምሰሶዎች ላይ ምክክር እየተደረገ ነው።
በመድረኩ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች በክብር እንግድነት ተገኝተው መልዕክት ማስተላለፋቸውን ከብልጽግና ፓርቲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.